class="content__text" ♀️አዳም የት ነህ?♀️ ከሩቅ ይሰማኛል የቤተስኪያን ደወል፣ ነብስን የሚያማልል ልብን የሚያባብል፣ እንደ አዲስ የሆነ እንደ አዋጅ የሆነ፣ ከቀን ሁሉ ጠዋት እሁድ የገነነ፣ ከእለት ሁሉ ግእዝ እሁድ የገነነ። ማለዳ ሰንጥቆ የሚያስገመግም ሰመመን መሳይ ድምፅ ከሩቅ የሚሰማ፣ ቀላቅሎ የያዘ የካህና ወረብ የካህናት ዜማ፣ ነፋስ የሚያመጣው አልፎ አልፎ ሽው የሚል፣ ተነስ ቀድስ የሚል አዳም የትነህ የሚል፣ አፍላ ጠዋት ሆኖ ሰማይ ከመሬት ጋር ሊላቀቅ ሲደማ፣ ሳሮች እንዳጤዙ ምንጩ ሳይነከር ቀኑ አዲስ እንዳለ፣ ከማለዳ ወፎች ድምፅ በልጦ፣ በነፋስ ከሚጋጩ የዛፎች ድምፅ በልጦ፣ ከሩሩሩቅ የሚመጣው የደወል ቤት ጩኸት የካህናት ዜማ፣ አየሩን ሰንጥቆ ንጋት ላይ ሲሰማ፣ ተንስ ኡ ሲል ገና ልቤን አሸፈተው፣ የቆየ ስሜቴን ማህሌት ያደረ የቄስ አፍ ሸተተው። ደሞ ያ ምስላቸው የቄሶቹ አቋቋም አደራደራቸው፣ የተክሌ ዝማሜ ሸንበቆ ስልታቸው፣ ባይነ ህሊናዬ ድቅን እያለብኝ ቅዝዝ ያደርገኛል፣ አዳም የት ነህ ይለኛል። እንዲህ ሲነጋጋ እሁድ ሊሆን ቀኑ ሰማይ ወገግ ሲል፣ ከደብሩ ምሶሶዎች የውስጠኛው ክፍል፣ ከታቦት ማደሪያው ያጎበር ክፍልፋይ ከጣሪያው ስዕል ስር፣ ልቆ ለመሰማት በሚጥር ትናጋ የዜማ ውድድር፣ ባንገታቸው ዙሪያ አግድም ባሰመረው የቄሶቹ ደም ስር፣ የሽቅብ ተገፍቶ የሚወጣው ዜማ፣ ጮሆ ንሮ ንሮ ልቆ ንሮ ንሮ ድንገት ፀጥ እያለ በሚቆየው ፋታ፣ የእጣነ ሞገሩ ወዲህ ወዲያ እንክርት ልዩ ቅጭልጭልታ፣ በመሃል ብቅ ሲል የሚሰጠው ሰላም የሚፈጥረው ደስታ፣ በጆሮዬ ነፍሶ አሁን እስኪመስል ድንግጥ ያደርገኛል፣ አዳም የት ነህ ይለኛል..? ወዲያው ደግሞ ድንገት እጣን በነካካ የካህናት መዳፍ፣ ተገልጦ ከተኛው የብራና መፅሃፍ፣ ከቀይ እና ጥቁር የፊደላት ቆሎ፣ ባይን እየዘገኑ ላንቃ ላይ ወርውሮ፣ ከሰማያት አንባ ከአራያም ሰፈር፣ ተጭኖ ደመና በዜማ መሳፈር፣ መሄድ መሄድ መሄድ መሄድ ያሰኘኛል፤ መዝለቅ ካድማሱ ስር፣ ከፀባኦት አንባ ከአረያም ቅጥር። ብቻ እንደጥንቱ ሁሉ ለመሆን ያማረኛል፣ ያኔ ቅስናዬ ሳይፈርስ ለብዙ ዘመናት በድንግልናዬ እንደፅናሁ ሁሉ ሰርክ ሳደገድግ ከደብር ሳልጠፋ፣ ከቅዳሴ ምላሽ ከፀበል ዳር ቆሜ፤ ድውያን ላሰልፍ ስደክም ስለፋ፣ ነብሴን ላለመልም ስጋዬን ሳደክም እንደኖርኩት ሁሉ እንደያኔው ሁሉ ለመሆን ያምረኛል! ደግሞ ባፍላነቴ በልጅነት ግዜ ማለዳ ነቅቼ፣ በሳር ውስጥ ባለ ቀጭን መንገድ በልጅ እግሬ ሮጬ፣ ከደብሩ ጉብታ ከደወል ቤት ኼጄ፤ በላብ የጠቆረ ገመድ ስወዘውዝ፣ እጄ አልደርስ እያለኝ በእግር ጣቴ ቆሜ፤ የቤቱን ወጋግራ ጉጥ ፈልጌ ስይዝ፣ ያ በልጅነት የሆንኩት አኳኋኔ ሁሉ ድቅን ይልብኛል፣ አዳም የት ነህ ይለኛል..? ዳሩ ምን ሊፈይድ የከሰመ እጣ፣ ግዜ አልፎበት ጥዑምነቱን ያጣ፣ አውራጅ ያጣ ቋንጣ..? መቼም ይህቺ ህይወት መስቀሏ ብዙ ነው፣ ታግላ ላትረታ ፀሯን ላታስገብረው፣ ካለም ጋር ግብግብ ትወዳለች፣ ተመንትፋ ልትሄድ ለኑሮም ሳትመች! ዛሬ ማ እኔ ቅስናዬ ፈርሶ፣ ድንግልናዬ ተድሶ፣ ጥምጣሜን ከፈታሁ ስንት ዘመን አለኝ፣ እንድያው ብቻ ድንገት የጥዋቱ ደወል ማለዳ ቀስቅሶ አዳም የት ነህ አለኝ..? እናም አውቆ የተኛን ሰው አይሰማም እንዲሉ፣ የዛሬውን ደወል አልሰማሁም አሉ..! የኔ ትዝታዎች የድሮ ቀኖቼ እንግዲህ ዝም በሉ፣ ልቤ እንዳደላችው ለስጋዬ አሁን ዓለም ቁብ እንዳላት፣ ልትመለስበት ለነብሴም ቀን አላት። ያ እስኪሆንላት ይኼ እንዳይብስባት፣ የድሮ ቀኖቼ እየነካካችሁ አትሁኑብኝ ጠላት! ልሸፋፈን እና አውቄ ልተኛበት። የዛሬውን ደወል አልሰማሁም ልበል፣ የደብር እድገቴ የቄስ ሁኔታዬ ትዝታዬም ዝም በል፣ ግን ከሩቅ ይሰማኛል የቤተስኪያን ደወል..! ንፋስ የሚያመጣው አልፎ አልፎ ሽው የሚል፣ ተነስ ቀድስ የሚል፣ አዳም የት ነህ የሚል...? #ቴዲ_አፍሮ 2001 ዓ.ም ተፃፈ
February 19, 2023
class="content__text" ቤተ ክርስቲያንን (ክርስቶስን) ማን ይመክራል...? ወዳጆቼ ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች አንደበታቸው የቱንም ያህል ቢጣፍጥ እንኳ ሁሉም ቃሎቻቸው የሽንገላ ናቸው። ይኼንን ለመረዳት ደግሞ ሩቅ ምስራቅን አልያም ምዕራባውያንን ለመፈተሽ መባዘን አይጠበቅብንም። የሀገራችንን የአራት አመት የምላስና የተግባር ውጤቶችን ማየት በቂ ነው። ለነርሱ (ለፖለቲከኞቹ) የሽንገላ ቃል እንደ ጽድቅ ነውና በእግዚአብሔር ካመጸው ጋ እንጂ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝ" ከሚል ጨዋ (ቅዱስ) ትውልድ ጋ የሚገጥም ባህሪይ የላቸውም። ሰሞኑን በቤተክርስቲያናችን ላይ ያሴረው አፈንጋጩ ኃይል እና ቅዱስ ሲኖዶሱ በሰላማዊ መንገድ ሊወያዩ የተቀመጡ ቢሆንም በግልጽ በሚዲያ እንደታየው ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጣልቃ በመግባት "አባቶችን እርሶም ይተዉ፥ እርሶም ይተዉ ልበ ሰፊ እንሁን" እያለ ጠቅለል አድርጎ ለመምከር ሲዳዳው ተስተውሏል። በተጨማሪም ማነው ከማህላቹ ገዳም ልግባ እያለ የሚጨቃጨቅ...? ጭቅጭቃቹ ለስልጣን ነው የሚሉ ኃይለ ቃሎችን ተጠቅሟ። ከነዚህም ውጪ ብዙ ነጥቦችን ቃል በቃል ማንሳት ይቻላል። ዳሩ ግን ለግንዛቤ በቂ ነውና ይኼንን እንደ አብነት ጠቅሰን ብናልፍ በቂነው። በጥቅሉ ቤተክርስቲያንን ሊመክሩ የማይችሉ ይልቁንም አባቶቻችን እግር ስር ቁጭ ብለው ጥበብን መማር ያለባቸው ግለሰቦች ካልመከርን አሉ። ይኽ እራሱን የቻለ ትልቅ የፖለቲካ ሴራ አለው። የኛ መበታተን፣ የቤተ ክርስቲያን መዳከም፣ የአባቶች መዋረድ ለነርሱ ትልቅ ትርፍ አለው። ግን ይኼ ቅዠት ብቻ ሆኖ ይቀራል። እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታዮች የተጋረጠብንን አደጋ በድል መሻገር የምንችለው የከበሩ አባቶቻችንን ቃል በመስማት ብቻ ነው። በተቻለ መጠን ፓለቲከኞቹ ለቤተክርስቲያናችን መፈራረስ ባዘጋጁልን ወጥመድ ላለመግባት በአንድ ልብ በአንድ አካል በአንድ መንፈስ መቆም አለብን። ጠላቶቻችን የዋዛ አይደሉም በአንድ የጥቃት ሙከራ ብቻ ተዋህዶን የማፍረስ ራዕያቸውን አያቆሙም። ለልጆቻችን (ለቀጣይ ትውልድ) ትክክለኛዋን የአባቶቻችንን ኃይማኖት ማውረስ ካለብን ዛሬ እኛ መስዋዕትነት መክፈል ይጠበቅብናል። ቋንቋን ሽፋን ያደረገው ይኽ ሴራ የቤተክርስቲያንን ይዞታ ከመንጠቅ እስከ ማፈራረስ እና እስከ መበታተን ድረስ ያለመ ትልቅ ሴይጣናዊ ሴራ ነው። ቅድስት ቤተክርስቲያን እራሷ ታስታርቃለች እንጂ የወጣት አስታራቂ መክሯት አያውቅም። እንኳን ሰውን ከሰው አመጸኛውን የሰውን ዘር ከክርስቶስ ጋ የምታስታርቅ አይደለችም እንዴ የኛ ቤተክርስቲያን...? በተረፈ ጃል! ኢየሱስ ክርስቶስ ባለበት ስሞ የሚሸጠው ይሁዳ እንዳለ ሁሉ እውነተኛውን እና ፍጹም ንጹህ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ወይንስ በርባንን ልልቀቅላቹ ብሎ ኃጣንን ከጻድቃን ጋ የሚያቆም፥ ኋላም ከደሙ ንጹህ ሳይሆን እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ የሚል ጲላጦስም አለ። ስለዚህ ይሁዳንም ጲላጦስንም መጠንቀቁ መልካም ነው። ጲላጦስ እውነትን መርምሮ አግኝቷት ነበር ዳሩ ግን እውነትን ገፋት። ይሁዳም የተገባ ሳይሆን በአምላኩ ተወዶ ለክብር ታጭቶ ነበር። እርሱ ግን ለክብር ያጨውን በሰላሳ ብር ለሞት አሳልፎ ሰጠው። ውግሩት፣ ግረፉት፣ ስቀሉትም ቤተመቅደሱንም (ሰውነቱንም) አፍርሱት ብሎ ሳቲሙን ይዞ ተሰወረ። ዛሬም ይሁዳ የዘመኑን ካባ ለብሶ በመሃላችን አለ። ጎበዝዬ ማንን መጠንቀቅ እንዳለብህ ካወክ ማንን መስማት እንዳለብኽ እኔ ባልነግርህም ይገባሃል። ቅድስት ቤተክርስቲያን የመከረችው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደመከረው ነው። ቅድስት ቤተክርስቲያንን የሳመ (የተሳለመ) ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሳመ ነው። እንዲሁ ቤተክርስቲያንን የከዳ እርሱ የተረገመ ነው ኢየሱስ ክርስቶስን ክዷልና። ✎✍ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
February 18, 2023
class="content__text" ከታች የተቀመጠው ሀሳብ የሁላችን ጽኑ አቋማችን ሊሆን ይገባል። ከዚህ ቀደም ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ( @teddyafromuzika ) ካስተላለፈው ተቀንጭቦ የወጣ። "...በዛሬው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶሱ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በተጠራው አዋጅ መላው ምዕመን ለሃይማኖቱ እና ለማተቡ በተጠንቀቅ እንዲቆም እና እስከመጨረሻውም የቅዱሳን አባቶቻችንን ድምፅ እንዲከተል በአፅንኦት ለማሳሰብ እወዳለሁ። (ቅጥፈት እና እብሪት ፍፃሜው ታላቅ ውድቀት ነው።)" ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በኢትዮጵያ ለዘለዓለም። #አንዲት_ቤተ_ክርስቲያን #አንድ_ሲኖዶስ #አንድ_ፓትርያርክ #eotc_one_holy_synod #one_church #one_patriarch #his_holiness_abune_mathias #oriental_orthodox
February 12, 2023
class="content__text" እግዚአብሔር መልካም ነገርን አደረገልን ደስም አለን!!! ለሆነልን፣ ለተደረገልን፣ ለሚደረግልንም ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔርን ታመሰግኑት ዘንድ ይገባል!! የኛ የሰው ልጆች በምድር ላይ ስንኖር እግዚአብሔር የሰጠንን ሰብዓዊ እና ተፈጥሯዊ መብቶች ምንም አይነት ኃይል መቀማት አይችልም!!! 💚💛❤️ 🙏🙏🙏 #አንዲት_ቤተ_ክርስቲያን #አንድ_ሲኖዶስ #አንድ_ፓትርያርክ #eotc_one_holy_synod #one_church #one_patriarch #his_holiness_abune_mathias #oriental_orthodox
February 12, 2023
class="content__text" በቅድሚያ የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም ከሰሞኑ በጥንታዊቷ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ላይ ሲካሄድ የነበረው ማዋከብ እና ቅዱስ ሲኖዶሱን የመከፋፈል ሴጣናዊ ስራ በጥብቅ እያወገዝኩ በዛሬው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶሱ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በተጠራው አዋጅ መላው ምዕመን ለሃይማኖቱ እና ለማተቡ በተጠንቀቅ እንዲቆም እና እስከመጨረሻውም የቅዱሳን አባቶቻችንን ድምፅ እንዲከተል በአፅንኦት ለማሳሰብ እወዳለሁ:: (ቅጥፈት እና እብሪት ፍፃሜው ታላቅ ውድቀት ነው።) ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) @teddyafromuzika
February 05, 2023
class="content__text" "ቆማችሁ ነፃነታችሁ ከሚረክስ ሞታችሁ ስማችሁ ይቀደስ...!" ኢትዮጵያዊ ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ "የአገሬ ጻድቅ ተዋሕዶ ያበቀለው ሰማዕቱ ጴጥሮስ ዛሬም ህያው ነው።" #አንዲት_ቤተ_ክርስቲያን #አንድ_ሲኖዶስ #አንድ_ፓትርያርክ #eotc_one_holy_synod #one_church #one_patriarch #his_holiness_abune_mathias #oriental_orthodox
February 05, 2023
class="content__text" የቅዱስ ሲኖዶስ መልዕክት! በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን! ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የጾምና የምሕላ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ "የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ! ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።" ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5 ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል። ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል። በመሆኑም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ጥር 26 ቀን 2015ዓ.ም. አዲስ አበባ #አንዲት_ቤተ_ክርስቲያን #አንድ_ሲኖዶስ #አንድ_ፓትርያርክ #eotc_one_holy_synod #one_church #one_patriarch #his_holiness_abune_mathias #oriental_orthodox
February 05, 2023
class="content__text" “መኑ ከመ ሄዋን እንደ ሚካኤል እናት፣ መኑ ከመ ሄዋን እንደ የማርያም እናት፣ መኑ ከመ ሄዋን እንደ የማሁስ እናት፣ መኑ ከመ ሄዋን እንደ ዘዳዊት እናት? ሁሌም አብራው ያለች እየሆነችው ብርታት ለብላቴናው ክብሩ ለልቡም ዘውድ ናት።” የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና የአርቲስት አምለሰት ሙጬ የአብራክ ክፋይ የሆኑት ልጆች 4 ሲሆኑ ሁለት ወንድ እንዲሁም ሁለት ሴቶች ናቸው። ስማቸውም እንደየ የልደት ቅደም ተከተላቸው፦ ሚካኤል ቴዎድሮስ፣ የማርያም ቴዎድሮስ፣ የማሁስ ቴዎድሮስ እና ዘዳዊት ቴዎድሮስ ይባላሉ። ማብራሪያ (ማስታወሻ) "መኑ ከመ ሄዋን" የሚለው የግዕዝ ቃል ወደ አማርኛ ሲተረጎም "ማን እንደ ሄዋን?" (ማን እንደ እናት) ማለት ነው።
January 19, 2023
class="content__text" Thank you so much, Atlanta! DMV, we can't wait to see you for new year's eve!
January 19, 2023
Similar accounts
Disclaimer
The data provides is not authorized by TikTok. We are not an official partner of TikTok.
Use of materials from the resource is permitted only with a link to our resource.
Contact