@teddyafronet

Teddy Afro

Unknown
class="content__text"
 ♀️አዳም የት ነህ?‍♀️

ከሩቅ ይሰማኛል የቤተስኪያን ደወል፣
ነብስን የሚያማልል ልብን የሚያባብል፣
እንደ አዲስ የሆነ እንደ አዋጅ የሆነ፣
ከቀን ሁሉ ጠዋት እሁድ የገነነ፣
ከእለት ሁሉ ግእዝ እሁድ የገነነ።

ማለዳ ሰንጥቆ የሚያስገመግም ሰመመን
መሳይ ድምፅ ከሩቅ የሚሰማ፣
ቀላቅሎ የያዘ የካህና ወረብ የካህናት ዜማ፣
ነፋስ የሚያመጣው አልፎ አልፎ ሽው የሚል፣
ተነስ ቀድስ የሚል አዳም የትነህ የሚል፣
አፍላ ጠዋት ሆኖ ሰማይ ከመሬት ጋር ሊላቀቅ ሲደማ፣
ሳሮች እንዳጤዙ ምንጩ ሳይነከር
ቀኑ አዲስ እንዳለ፣
ከማለዳ ወፎች ድምፅ በልጦ፣
በነፋስ ከሚጋጩ የዛፎች ድምፅ በልጦ፣
ከሩሩሩቅ የሚመጣው የደወል ቤት ጩኸት የካህናት ዜማ፣
አየሩን ሰንጥቆ ንጋት ላይ ሲሰማ፣
ተንስ ኡ ሲል ገና ልቤን አሸፈተው፣
የቆየ ስሜቴን ማህሌት ያደረ የቄስ አፍ ሸተተው።
ደሞ ያ ምስላቸው የቄሶቹ አቋቋም አደራደራቸው፣
የተክሌ ዝማሜ ሸንበቆ ስልታቸው፣
ባይነ ህሊናዬ ድቅን እያለብኝ ቅዝዝ ያደርገኛል፣
አዳም የት ነህ ይለኛል።

እንዲህ ሲነጋጋ እሁድ ሊሆን ቀኑ ሰማይ ወገግ ሲል፣
ከደብሩ ምሶሶዎች የውስጠኛው ክፍል፣
ከታቦት ማደሪያው ያጎበር ክፍልፋይ ከጣሪያው ስዕል ስር፣
ልቆ ለመሰማት በሚጥር ትናጋ የዜማ ውድድር፣
ባንገታቸው ዙሪያ አግድም ባሰመረው የቄሶቹ ደም ስር፣
የሽቅብ ተገፍቶ የሚወጣው ዜማ፣
ጮሆ ንሮ ንሮ ልቆ ንሮ ንሮ ድንገት ፀጥ
እያለ በሚቆየው ፋታ፣
የእጣነ ሞገሩ ወዲህ ወዲያ እንክርት ልዩ ቅጭልጭልታ፣
በመሃል ብቅ ሲል የሚሰጠው ሰላም የሚፈጥረው ደስታ፣
በጆሮዬ ነፍሶ አሁን እስኪመስል ድንግጥ ያደርገኛል፣
አዳም የት ነህ ይለኛል..?

ወዲያው ደግሞ ድንገት እጣን በነካካ የካህናት መዳፍ፣
ተገልጦ ከተኛው የብራና መፅሃፍ፣
ከቀይ እና ጥቁር የፊደላት ቆሎ፣
ባይን እየዘገኑ ላንቃ ላይ ወርውሮ፣
ከሰማያት አንባ ከአራያም ሰፈር፣
ተጭኖ ደመና በዜማ መሳፈር፣
መሄድ መሄድ መሄድ መሄድ ያሰኘኛል፤
መዝለቅ ካድማሱ ስር፣
ከፀባኦት አንባ ከአረያም ቅጥር።

ብቻ እንደጥንቱ ሁሉ ለመሆን ያማረኛል፣
ያኔ ቅስናዬ ሳይፈርስ ለብዙ ዘመናት
በድንግልናዬ እንደፅናሁ ሁሉ ሰርክ ሳደገድግ ከደብር ሳልጠፋ፣
ከቅዳሴ ምላሽ ከፀበል ዳር ቆሜ፤
ድውያን ላሰልፍ ስደክም ስለፋ፣
ነብሴን ላለመልም ስጋዬን ሳደክም እንደኖርኩት ሁሉ
እንደያኔው ሁሉ ለመሆን ያምረኛል!
ደግሞ ባፍላነቴ በልጅነት ግዜ ማለዳ ነቅቼ፣
በሳር ውስጥ ባለ ቀጭን መንገድ በልጅ እግሬ ሮጬ፣
ከደብሩ ጉብታ ከደወል ቤት ኼጄ፤
በላብ የጠቆረ ገመድ ስወዘውዝ፣
እጄ አልደርስ እያለኝ በእግር ጣቴ ቆሜ፤
የቤቱን ወጋግራ ጉጥ ፈልጌ ስይዝ፣
ያ በልጅነት የሆንኩት አኳኋኔ ሁሉ ድቅን ይልብኛል፣
አዳም የት ነህ ይለኛል..?

ዳሩ ምን ሊፈይድ የከሰመ እጣ፣
ግዜ አልፎበት ጥዑምነቱን ያጣ፣
አውራጅ ያጣ ቋንጣ..?
መቼም ይህቺ ህይወት መስቀሏ ብዙ ነው፣
ታግላ ላትረታ ፀሯን ላታስገብረው፣
ካለም ጋር ግብግብ ትወዳለች፣
ተመንትፋ ልትሄድ ለኑሮም ሳትመች!
ዛሬ ማ እኔ ቅስናዬ ፈርሶ፣
ድንግልናዬ ተድሶ፣
ጥምጣሜን ከፈታሁ ስንት ዘመን አለኝ፣
እንድያው ብቻ ድንገት የጥዋቱ ደወል ማለዳ
ቀስቅሶ አዳም የት ነህ አለኝ..?
እናም አውቆ የተኛን ሰው አይሰማም እንዲሉ፣
የዛሬውን ደወል አልሰማሁም አሉ..!

የኔ ትዝታዎች የድሮ ቀኖቼ እንግዲህ ዝም በሉ፣
ልቤ እንዳደላችው ለስጋዬ አሁን ዓለም ቁብ እንዳላት፣
ልትመለስበት ለነብሴም ቀን አላት።
ያ እስኪሆንላት ይኼ እንዳይብስባት፣
የድሮ ቀኖቼ እየነካካችሁ አትሁኑብኝ ጠላት!
ልሸፋፈን እና አውቄ ልተኛበት።
የዛሬውን ደወል አልሰማሁም ልበል፣
የደብር እድገቴ የቄስ ሁኔታዬ ትዝታዬም ዝም በል፣
ግን ከሩቅ ይሰማኛል የቤተስኪያን ደወል..!
ንፋስ የሚያመጣው አልፎ አልፎ ሽው የሚል፣
ተነስ ቀድስ የሚል፣
አዳም የት ነህ የሚል...?

 #ቴዲ_አፍሮ

2001 ዓ.ም ተፃፈ

class="content__text" ♀️አዳም የት ነህ?‍♀️ ከሩቅ ይሰማኛል የቤተስኪያን ደወል፣ ነብስን የሚያማልል ልብን የሚያባብል፣ እንደ አዲስ የሆነ እንደ አዋጅ የሆነ፣ ከቀን ሁሉ ጠዋት እሁድ የገነነ፣ ከእለት ሁሉ ግእዝ እሁድ የገነነ። ማለዳ ሰንጥቆ የሚያስገመግም ሰመመን መሳይ ድምፅ ከሩቅ የሚሰማ፣ ቀላቅሎ የያዘ የካህና ወረብ የካህናት ዜማ፣ ነፋስ የሚያመጣው አልፎ አልፎ ሽው የሚል፣ ተነስ ቀድስ የሚል አዳም የትነህ የሚል፣ አፍላ ጠዋት ሆኖ ሰማይ ከመሬት ጋር ሊላቀቅ ሲደማ፣ ሳሮች እንዳጤዙ ምንጩ ሳይነከር ቀኑ አዲስ እንዳለ፣ ከማለዳ ወፎች ድምፅ በልጦ፣ በነፋስ ከሚጋጩ የዛፎች ድምፅ በልጦ፣ ከሩሩሩቅ የሚመጣው የደወል ቤት ጩኸት የካህናት ዜማ፣ አየሩን ሰንጥቆ ንጋት ላይ ሲሰማ፣ ተንስ ኡ ሲል ገና ልቤን አሸፈተው፣ የቆየ ስሜቴን ማህሌት ያደረ የቄስ አፍ ሸተተው። ደሞ ያ ምስላቸው የቄሶቹ አቋቋም አደራደራቸው፣ የተክሌ ዝማሜ ሸንበቆ ስልታቸው፣ ባይነ ህሊናዬ ድቅን እያለብኝ ቅዝዝ ያደርገኛል፣ አዳም የት ነህ ይለኛል። እንዲህ ሲነጋጋ እሁድ ሊሆን ቀኑ ሰማይ ወገግ ሲል፣ ከደብሩ ምሶሶዎች የውስጠኛው ክፍል፣ ከታቦት ማደሪያው ያጎበር ክፍልፋይ ከጣሪያው ስዕል ስር፣ ልቆ ለመሰማት በሚጥር ትናጋ የዜማ ውድድር፣ ባንገታቸው ዙሪያ አግድም ባሰመረው የቄሶቹ ደም ስር፣ የሽቅብ ተገፍቶ የሚወጣው ዜማ፣ ጮሆ ንሮ ንሮ ልቆ ንሮ ንሮ ድንገት ፀጥ እያለ በሚቆየው ፋታ፣ የእጣነ ሞገሩ ወዲህ ወዲያ እንክርት ልዩ ቅጭልጭልታ፣ በመሃል ብቅ ሲል የሚሰጠው ሰላም የሚፈጥረው ደስታ፣ በጆሮዬ ነፍሶ አሁን እስኪመስል ድንግጥ ያደርገኛል፣ አዳም የት ነህ ይለኛል..? ወዲያው ደግሞ ድንገት እጣን በነካካ የካህናት መዳፍ፣ ተገልጦ ከተኛው የብራና መፅሃፍ፣ ከቀይ እና ጥቁር የፊደላት ቆሎ፣ ባይን እየዘገኑ ላንቃ ላይ ወርውሮ፣ ከሰማያት አንባ ከአራያም ሰፈር፣ ተጭኖ ደመና በዜማ መሳፈር፣ መሄድ መሄድ መሄድ መሄድ ያሰኘኛል፤ መዝለቅ ካድማሱ ስር፣ ከፀባኦት አንባ ከአረያም ቅጥር። ብቻ እንደጥንቱ ሁሉ ለመሆን ያማረኛል፣ ያኔ ቅስናዬ ሳይፈርስ ለብዙ ዘመናት በድንግልናዬ እንደፅናሁ ሁሉ ሰርክ ሳደገድግ ከደብር ሳልጠፋ፣ ከቅዳሴ ምላሽ ከፀበል ዳር ቆሜ፤ ድውያን ላሰልፍ ስደክም ስለፋ፣ ነብሴን ላለመልም ስጋዬን ሳደክም እንደኖርኩት ሁሉ እንደያኔው ሁሉ ለመሆን ያምረኛል! ደግሞ ባፍላነቴ በልጅነት ግዜ ማለዳ ነቅቼ፣ በሳር ውስጥ ባለ ቀጭን መንገድ በልጅ እግሬ ሮጬ፣ ከደብሩ ጉብታ ከደወል ቤት ኼጄ፤ በላብ የጠቆረ ገመድ ስወዘውዝ፣ እጄ አልደርስ እያለኝ በእግር ጣቴ ቆሜ፤ የቤቱን ወጋግራ ጉጥ ፈልጌ ስይዝ፣ ያ በልጅነት የሆንኩት አኳኋኔ ሁሉ ድቅን ይልብኛል፣ አዳም የት ነህ ይለኛል..? ዳሩ ምን ሊፈይድ የከሰመ እጣ፣ ግዜ አልፎበት ጥዑምነቱን ያጣ፣ አውራጅ ያጣ ቋንጣ..? መቼም ይህቺ ህይወት መስቀሏ ብዙ ነው፣ ታግላ ላትረታ ፀሯን ላታስገብረው፣ ካለም ጋር ግብግብ ትወዳለች፣ ተመንትፋ ልትሄድ ለኑሮም ሳትመች! ዛሬ ማ እኔ ቅስናዬ ፈርሶ፣ ድንግልናዬ ተድሶ፣ ጥምጣሜን ከፈታሁ ስንት ዘመን አለኝ፣ እንድያው ብቻ ድንገት የጥዋቱ ደወል ማለዳ ቀስቅሶ አዳም የት ነህ አለኝ..? እናም አውቆ የተኛን ሰው አይሰማም እንዲሉ፣ የዛሬውን ደወል አልሰማሁም አሉ..! የኔ ትዝታዎች የድሮ ቀኖቼ እንግዲህ ዝም በሉ፣ ልቤ እንዳደላችው ለስጋዬ አሁን ዓለም ቁብ እንዳላት፣ ልትመለስበት ለነብሴም ቀን አላት። ያ እስኪሆንላት ይኼ እንዳይብስባት፣ የድሮ ቀኖቼ እየነካካችሁ አትሁኑብኝ ጠላት! ልሸፋፈን እና አውቄ ልተኛበት። የዛሬውን ደወል አልሰማሁም ልበል፣ የደብር እድገቴ የቄስ ሁኔታዬ ትዝታዬም ዝም በል፣ ግን ከሩቅ ይሰማኛል የቤተስኪያን ደወል..! ንፋስ የሚያመጣው አልፎ አልፎ ሽው የሚል፣ ተነስ ቀድስ የሚል፣ አዳም የት ነህ የሚል...? #ቴዲ_አፍሮ 2001 ዓ.ም ተፃፈ

February 19, 2023

Disclaimer

The data provides is not authorized by TikTok. We are not an official partner of TikTok.

Use of materials from the resource is permitted only with a link to our resource.

Copyright © 2025 insiflow.com